ውሃ ለሰውነታችን ጤናማ አሠራር ከምንፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲሆን የምርምር ውጤቶች እንደሚያሳዩት 60 በመቶው ሰውነታችን ከውኃ የተሠራ ነው። ስለዚህ በሰውነታችን ውስጥ በቂ ውሃ ማግኘታችን በሰውነታችን አሠራር ውስጥ ትልቅ ሚና ስለሚጫወት በቀን ውስጥ ሰውነታችን የሚፈልገውን ያህል ውሃ መጠጣት አለብን። እስከ ስድስት ብርጭቆ ውሃ መጠጣት ይመከራል ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች ምንም የተወሰነ ገደብ እንደሌለ ይናገራሉ. የኩላሊት፣የጉበት፣የልብና የታይሮይድ ችግር በሚኖርበት ጊዜ የምንጠጣውን የውሃ መጠን እንዲጨምር ይመከራል። ይሁን እንጂ አብዛኛው ሰው ሰውነት በሚፈልገው መጠን በቂ ውሃ መጠጣትን ለመለማመድ ይከብዳቸዋል።
መጠጥ ውሃ ጥቅሞች
1.
የሰውነት ሙቀትን መቆጣጠር
2.
ሰውነታችንን በቂ ኦክስጅን ማቅረብ
3.
የመተንፈሻ አካላትን መርዳት
4.
የአጥንት መገጣጠሚያዎችን ማለስለስ
5.
የደም ግፊትን መቆጣጠር
6.
የሰውነት ቆሻሻን በላብ ማስወገድ
7.
ጤናማ ቆዳ መኖር
8 ትክክለኛ የምግብ መፈጨት ሂደት እንዲኖርዎት
9.
ሰውነት በውስጡ በመሟሟት ንጥረ ምግቦችን እንዲጠቀም ማድረግ
10.
የኩላሊት ጠጠርን እና ተፅዕኖዎችን ለመከላከል
11.
የሰውነት ክብደትን ለማስተካከል
12.
የሆድ ድርቀትን ለመከላከል
13. የውስጥ አካላትን ከአደጋ ለመጠበቅ
ዋቢ መፀሀፍት
1.https://www.health.harvard.edu/staying-healthy/how-much-water-should-you-drink
2.https://www.medicalnewstoday.com/articles/290814


0 Comments